ያንጎ ኢትዮጵያ 50 አዳዲስ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ ሥራ አስገባ
ያንጎ ኢትዮጵያ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት 50 አዳዲስ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ አገልግሎት አስገብቷል።
ከዳሽን ባንክ እና ከኤለጋንስ አስመጪ ጋር በመተባበር የቀረቡት እነዚህ መኪኖች፣ በያንጎ መተግበሪያ ውስጥ "ኮምፎርት ፕላስ" በተባለው ምድብ ለተጠቃሚዎች ምቹና ፈጣን የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣሉ።
ይህ እርምጃ በያንጎ መተግበሪያ ላይ የሚገኙ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ከፍ ያደርገዋል።
ኩባንያው ለወደፊቱም ከተለያዩ አጋሮች ጋር በመስራት፣ በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቁጥር ለመጨመር እና ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎትን በስፋት ለማዳረስ እቅድ እንዳለው አስታውቋል።
#afromekina
Loading content...
