የዓለማችን ትልቁ የኤሌክትሪክ አውሮፕላን
በአሜሪካ ሰማይ ላይ የተሳካ በረራ አደረገ
አውሮፓ የሰራችው የዓለማችን ትልቁ የኤሌክትሪክ አውሮፕላን (X1) በአሜሪካ ኒውዮርክ ሰማይ ላይ ለ27 ደቂቃዎች በተሳካ ሁኔታ በረረ።
የስውዲኑ 'ሃርት ኤሮስፔስ' ኩባንያ የነደፈው ይህ አውሮፕላን በረራውን ለማድረግ 5 ዶላር የሚጠጋ የኤሌክትሪክ ኃይል ብቻ መጠቀሙ ተጠቁሟል።
የዚህ አውሮፕላን ዋና ምርት የሆነው ES-30 የተባለው ባለ 30 መቀመጫ አውሮፕላን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ብቻ የሚሰራ ሳይሆን፣ ባትሪ ሲያልቅ የሚያገለግል የነዳጅ ማስተካከያ (Hybrid) የተገጠመለት ነው።
አውሮፕላኑ በባትሪ ብቻ 200 ኪሎ ሜትር፣ ከነዳጅ ማስተካከያው ጋር ደግሞ እስከ 800 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችል ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 2031 አገልግሎት ለመጀመር ታቅዷል።
ዩናይትድ ኤርላይንስ እና ኤር ካናዳን ጨምሮ በርካታ አየር መንገዶች 9.4 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
#afromekina
Loading content...
