የዓለም ነዳጅ ክምችት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ተባለ
የሳኡዲ አራምኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሚን ናሰር እንደገለጹት፣ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ክምችቶች አሳሳቢ በሆነ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ሀገራት በገበያው ላይ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት የድንገተኛ ጊዜ ክምችታቸውን ወደ ገበያ እያወጡ ቢሆንም፣ ይህ እርምጃ ለጊዜው እፎይታ ከመስጠት ባለፈ የመሰረታዊ አቅርቦት እና ፍላጎት አለመመጣጠን ችግርን በዘላቂነት አይፈታውም።
ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እና በነዳጅ ገበያ ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ ጫና ለማቃለል ብቸኛው መንገድ የሆርሙዝ ሰርጥን ሙሉ በሙሉ ክፍት መሆን እንደሆነ ተጠቅሷል።
በሌላ በኩል፣ የጂ-7 (G7) ሀገራት የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥሪ ተከተሎ የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት 100 ሚሊዮን በርሜል የዲዜል ክምችት ወደ ገበያ ለመልቀቅ ተስማምተዋል።
ሆኖም የመጓጓዣ መስመሮች ካልተከፈቱ የነዳጅ እጥረት ስጋቱ ተባብሶ እንደሚቀጥል ተስግቷል።
#afromekina
Loading content...
