የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከ3 በመቶ በላይ በሆነ ከፍተኛ መጠን መውረዱ ተሰማ
ይህ የሆነው የአሜሪካው ፕሬስዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የኢራኑ ፕሬስዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጦርነቱን ለማቆም እና በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ በኩል የሚደረገውን የመርከብ ትራንስፖርት መልሶ ለመጀመር የሚያስችለውን ስምምነት ማፅደቃቸውን ተከትሎ ነው።
ዛሬ ጠዋት ላይ በተመዘገበው መረጃ መሠረት፥ የአሜሪካው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት (WTI) የነዳጅ ዋጋ የቀነሰ ሲሆን፥ ዓለም አቀፍ መነሻ የሆነው የሰሜን ባህር ብሬንት የነዳጅ ዋጋ ደግሞ በ3.02 በመቶ ማሽቆልቆሉ ታይቷል።
በዚህም መሠረት በአሁኑ ወቅት አንድ በርሜል የቦሬንት ነዳጅ በ77 ዶላር ከ15 ሳንቲም እየተሸጠ እንደሚገኝ ታውቋል።
ስምምነቱ በዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦት ላይ የነበረውን ስጋት በመቅረፍ የዋጋ መረጋጋት እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
#afromekina
Loading content...
