ቮልስዋገን የ100 ሺህ ሰራተኞች ቅነሳ ሊያደርግ ነው ተባለ
የጀርመኑ ግዙፍ የመኪና አምራች በታሪኩ ትልቁ የተባለውን ታሪካዊ መዋቅራዊ ለውጥ በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ እስከ 100 ሺህ የሚደርሱ ሰራተኞችን ሊቀንስ እንደሚችል ዋና ስራ አስፈጻሚው ኦሊቨር ብሉሜ አረጋግጠዋል።
እንደ ዮሮ ኒውስ ዘገባ ኩባንያው ከዚህ ቀደም በጀርመን ብቻ 50 ሺህ ሰራተኞችን ለመቀነስ አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን የቅነሳው እቅድ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።
ለዚህ አስደንጋጭ ውሳኔ ዋነኛ መንስኤ የሆነው የኩባንያው የትርፍ መጠን ማሽቆልቆል እና በተለይም በቻይና ገበያ ያለው ሽያጭ በ26 በመቶ በመቀነሱ ነው።
እንደ ስራ አስፈጻሚው ገለጻ፣ የቮልስዋገን የስራ የማስኬጃ ወጪ ከተወዳዳሪዎቹ በ20 በመቶ ከፍ ያለ በመሆኑ ወጪን መቀነስ ግድ ሆኗል።
የቻይና መኪና አምራቾች እያደረጉት ያለው ጠንካራ ውድድርም በአውሮፓውያን ኩባንያዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሯል።
ይሁንና አንዳንድ ተንታኞች ይህ ቁጥር ለሰራተኛ ማህበራት ድርድር የቀረበ ስልት ሊሆን ስለሚችል የመጨረሻው የቅነሳ መጠን ሊያንስ እንደሚችል ይገምታሉ።
#afromekina
Loading content...
