የመንግስት ሰሌዳ ያላቸው ነባር ተሽከርካሪዎች እስከ ጥቅምት 30 ሰሌዳቸውን በአዲሱ እንዲቀይሩ ትዕዛዝ ተሰጠ
በፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት ስር የሚገኙና “ኮድ 4” የመንግስት መለያ ሰሌዳ ያላቸው ነባር ተሽከርካሪዎች እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ሰሌዳቸውን በአዲሱ “ETH” መለያ እንዲቀይሩ ተወስኗል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አዲሱን “ETH” የተሽከርካሪ መለያ ቁጥር ሰሌዳ ከሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአዲስ ተሽከርካሪዎች ምዝገባ ተግባራዊ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የዚሁ አሰራር አካል የሆነው የነባር የመንግስት ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ቅያሬ መጀመሩ ተገልጿል።
የሎጀስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው የኮድ 4 ነባር ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ቅያሬ አገልግሎት ከጥቅምት 17 ቀን ጀምሮ መሰጠት የጀመረ ሲሆን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ ይቆያል።
በመሆኑም የሚመለከታቸው የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት የተሽከርካሪ ፋይላቸው በሚገኝበት የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በአካል በመቅረብ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሳይዘገዩ የሰሌዳ ቅያሬ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ምስል በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) የተሰራ!!
#afromekina
Loading content...
