የአሜሪካ መንግሥት 53.3 ሚ. በርሜል
ነዳጅ ለኩባንያዎች ለማበደር ወሰነ
በአሜሪካ፣ በእስራኤልና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የናረውን የነዳጅ ዋጋ ለማርገብ የትራምፕ አስተዳደር 53.3 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ለኃይል አምራች ኩባንያዎች በብድር መልክ ለመስጠት መወሰኑን የአሜሪካ ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ይህ እርምጃ አሜሪካ ከዓለም አቀፍ የኢነርጂ ኤጀንሲ አባል ሀገራት ጋር በመሆን በድምሩ 400 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ለገበያ ለማቅረብ ያደረገችው ስምምነት አካል ሲሆን፣ እንደ ኤክሶን ሞቢል እና ማራቶን ያሉ ዘጠኝ ግዙፍ ኩባንያዎች በዚህ የብድር ስምምነት ውስጥ ተካተዋል።
መንግሥት ነዳጁን ለኩባንያዎቹ የሚያበድረው በልዩ ስምምነት ሲሆን፣ ተበዳሪዎቹ ኩባንያዎች ነዳጁን ሲመልሱ የወሰዱትን መጠን ብቻ ሳይሆን እስከ 24 በመቶ የሚደርስ ተጨማሪ ነዳጅ (እንደ ወለድ) ጨምረው መመለስ ይኖርባቸዋል። በአሁኑ ወቅት በሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ምክንያት በአሜሪካ አንድ ጋሎን ነዳጅ በአማካይ 4.52 ዶላር እየተሸጠ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህ አዲሱ አሰራር የታክስ ከፋዩን ገንዘብ ሳይነካ የነዳጅ አቅርቦትን በመጨመር ገበያውን ለማረጋጋት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
#afromekina
Loading content...
