አሜሪካ የ4.5 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ መሙያ የጦር አውሮፕላኖችን ለኳታር ልትሸጥ መሆኑን አጸደቀች
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስከ አራት የሚደርሱ «KC-46A» የአየር ላይ ነዳጅ መሙያ የጦር አውሮፕላኖችን እና ተዛማጅ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በ4.5 ቢሊዮን ዶላር ለኳታር ለመሸጥ የቀረበውን እቅድ ማፅደቁን አስታወቀ።
ሽያጩ ስምንት «PW4062» ተርቦፋን ሞተሮችን የሬዳር ማስጠንቀቂያ ተቀባዮችን የሌዘር አስተላላፊዎችን እና ሌሎች አቪዬሽን ነክ መሳሪያዎችን ያካትታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ይህ ሽያጭ ኳታር በቀጠናው ደህንነት መጠበቅ ላይ የምታደርገውን ሚና የሚያጠናክር ሲሆን «በቀጠናው ያለውን መሰረታዊ የወታደራዊ ኃይል ሚዛን አይቀይረውም» ብሏል።
የ«KC-46A» አውሮፕላኖች የኳታር አየር ኃይል የጦር ጄቶቹ በአየር ላይ እያሉ ነዳጅ እንዲሞሉ በማድረግ የረጅም ርቀት ወታደራዊ ስምሪት የማድረግ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድጉለት ተጠቅሷል።
#afromekina