እንግሊዝ ለሳዑዲ አረቢያ የአየር ላይ ነዳጅ መሙላት ድጋፍ ለመስጠት ተስማማች
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሃም ሳዑዲ አረቢያ ላቀረበችው የአጭር ጊዜ የመከላከያ ድጋፍ ጥያቄ መስማማታቸውን ገልፀዋል ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔው ሳዑዲ አረቢያ ጥቃት እየደረሰባት በመሆኑና በክልሉ ያሉ ወሳኝ መተላለፊያ መስመሮች ክፍት ሆነው እንዲቀጥሉ ለማድረግ መሆኑ አስረድተዋል።
የእንግሊዝ ድጋፍ ለሳዑዲ የጦር አውሮፕላኖች በአየር ላይ ነዳጅ እንዲሞሉ በማድረግ የመከላከያ ተልዕኮዎችን ለማከናወን የሚያግዝ ነው።
እንግሊዝ እና ሳዑዲ አረቢያ ለበርካታ ዓመታት የቅርብ ወታደራዊ አጋሮች ሲሆኑ፣ እንግሊዝ ለሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የጦር መሣሪያ አቅራቢ ሀገር ናት ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
#afromekina
Loading content...
