ኡጋንዳ በቅርቡ ለገበያ ለምታቀርበው የነዳጅ ምርት 'ፐርል ስዊት' የሚል ስያሜ ሰጠች
🇺🇬 "ስዊት" የሚለው ስያሜ የነዳጁን ዝቅተኛ የሰልፈር መጠን የሚያመለክት፤ "ፐርል" ደግሞ ለኡጋንዳ “ፐርል ኦፍ አፍሪካ” መጠሪያ እውቅና ለመስጠት እንደሆነ ፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ስያሜውን ይፋ ባደረጉበት መርኃ-ግብር ላይ አብራርተዋል።
🛢 ኡጋንዳ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ነዳጁን ለሽያጭ ማውጣት እንደምትጀምር ትጠብቃለች። "ፐርል ስዊት" የተሰኘው የድፍድፍ ነዳጅ 1,443 ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው የምሥራቅ አፍሪካ የድፍድፍ ነዳጅ ቧንቧ መስመር ወደ ታንዛኒያ ታንጋ ወደብ ይጓጓዛል።
"የተረጋገጠው 6.5 ቢሊዮን በርሜል ነዳጅ የአልበርት ሐይቅን 40% ብቻ የሚሸፍን ነው። 60% የሚሆነው አካባቢ ገና ፍለጋ አልተደረገበትም" ሲሉ ሙሴቬኒ ተናግረዋል።
👉 ኡጋንዳ ከ "ኪንግፊሸር" የነዳጅ ማውጫ የሚወጣውን ጋዝ በከንቱ አታቃጥልም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ጋዙ ለኃይል ማመንጫ እና ለፈሳሽ የምግብ ማብሰያ ጋዝ ማምረቻ እንደሚውል አረጋግጠዋል።
#afromekina
Loading content...
