ትራምፕ ከቬንዙዌላ የሚገኘው የነዳጅ ገቢ በመቶ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር እንደሚያስገኝ ተናገሩ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደተናገሩት ከቬንዙዌላ የሚገኘው የነዳጅ ገቢ በቅርቡ በመቶ ቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ይሆናል።አሜሪካም በሀገሪቱ ላደረገችው ወታደራዊ ዘመቻ ያወጣችውን ወጪ በብዙ እጥፍ መልሳ አግኝታለች ብለዋል።
በፈረንጆቹ 2026 ዓመት በተከበረው የብሔራዊ የቀድሞ ዘማቾች ቀን ስነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በእኛ በኩል ቬንዙዌላ አለችን፤ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የሚያወጣ ነዳጅ እና ሌሎች የተለያዩ ነገሮችን እያወጣን ነው፤ ይህም በቅርቡ በመቶ ቢሊዮኖች ይደርሳል ነው ያሉት።
ማንም ሰው እንደዚህ ያለ ነገር አይቶ አያውቅም፤ ለጦርነቱ ያወጣነውንም ወጪ አስቀድመን በብዙ እጥፍ መልሰናል ሲሉ ተናግረዋል። በየሳምንቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የበርሜል ነዳጅ ከቬንዙዌላ እየወጣ መሆኑን እና ይህም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ገቢ እያስገኘ መሆኑን ትራምፕ ገልጸዋል።
#afromekina
Loading content...
