ትራምፕ በግሪንላንድ ከፍተኛ የነዳጅ ፍለጋ ስራ ሊጀመር መሆኑን ገለጹ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰጡት መግለጫ በግሪንላንድ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ስራ ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
የአሜሪካን ቀጥተኛ ዝርዝር ሁኔታን ያልገለፁት ፕሬዚዳንቱ በግሪንላንድ ከፍተኛ የነዳጅ፣ ጋዝ እና ማዕድን ፍለጋ ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።የአርክቲክ ደሴቲቱ ለአሜሪካ እና ለአውሮፓ ደህንነት ስልታዊ ቦታ መሆኗንም አክለዋል።
ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት በቀላሉ ሊገኝ የሚችለው የነዳጅ መጠን በዓለም ላይ ካሉ ከማንኛውም ቦታዎች በላቀ ሁኔታ እጅግ ብዙ ነው ብለዋል። ዋሽንግተን የኮፐንሃገንን ስልታዊ ጥቅም ያላትን የአርክቲክ ግዛት በኃይል ለመውሰድ ትራምፕ ካስፈራሩ በኋላ ከግሪንላንድ እና ከዴንማርክ መሪዎች ጋር የጸጥታ ስምምነት ተፈራርማለች።
ባለፈው ነሃሴ ወር አንድ የአሜሪካ የነዳጅ ኩባንያ በምስራቃዊ ግሪንላንድ ርቆ በሚገኝ ቀጠና ውስጥ ያደረገው የመጀመሪያ ደረጃ ዝግጅት በደሴቲቱ ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ዘንድ ስጋትን ፈጥሮ ነበር።
#afromekina
Loading content...
