የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን ተከትሎ ጨምሮ በርካታ ከተሞች የትራንስፖርት አድማ እና ተቃውሞ ተቀሰቀሰ!
በኬንያ ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን ተከትሎ ሰኞ ዕለት በአገር አቀፍ ደረጃ የሕዝብ ትራንስፖርት አድማ እና ተቃውሞ እየተደረገ ነው። ይህም በዋና ዋና ከተሞች፣ ናይሮቢን ጨምሮ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ተጓዦችን መንገድ ያደናቀፈ ሲሆን በንግድ ተቋማት እና በትምህርት ቤቶች ላይም መስተጓጎል ፈጥሯል።
የዛሬው ተቃውሞ የተነሳው የኢነርጂ እና ነዳጅ ቁጥጥር ባለሥልጣን (EPRA) በቅርቡ ያደረገውን የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ ተከትሎ ሲሆን፥ ባለሥልጣኑ በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ ከመጣው ውጥረት እና የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ላይ ከደረሰው መስተጓጎል ጋር በተያያዘ የዓለም አቀፍ የነዳጅ አቅርቦት መቋረጥን በምክንያትነት በመጥቀስ የችርቻሮ ነዳጅ ዋጋን ከ20 በመቶ በላይ ጨምሯል።
ሮይተርስ እንደዘገበው በናይሮቢ የሱፐር ቤንዚን ዋጋ በአንድ ሊትር ወደ 214 የኬንያ ሺሊንግ አካባቢ የደረሰ ሲሆን፥ ናፍጣ ደግሞ ወደ 243 ሺሊንግ ገደማ አቅቷል።
ቢቢሲ በበኩሉ ከትራንስፖርት ዘርፍ አሊያንስ ጋር ግንኙነት ያላቸው አሽከርካሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ አድማ መጀመራቸውን የዘገበ ሲሆን፥ አድመኞቹም ጎማዎችን በማቃጠል መንገዶችን ዘግተዋል ብሏል ።
ፖሊስ በበኩሉ በተለያዩ አካባቢዎች አስለቃሽ ጋዝ በመተኮስ ምላሽ ሰጥቷል። የትራንስፖርት መዘጋቱ ዋና ዋና የትራንስፖርት መስመሮችን ያሽመደመደ ሲሆን፣በርካታ ተጓዦች ወደ ሥራ ቦታቸው ረጅም ርቀት በእግራቸው ለመጓዝ ተገደዋል።
#afromekina
Loading content...
