የቤንዚን መኪናን ወደ ሙሉ ኤሌትሪክ ተሽከርካሪነት መቀየሩን ዩኒቨርስቲው ገለፀ
በቤንዚን የሚንቀሳቀስ የ ' Sandstorm S24 ' ፒክአፕ ተሽከርካሪን ወደ ሙሉ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ በተሳካ ሁኔታ መቀየሩን የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ኮሌጅ አሳውቋል።
ፕሮጀክቱ በዩኒቨርሲቲው የአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ተመራማሪዎች የተመራ ሲሆን ተሽከርካሪውን የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ነው የሰጠው።
ተሽከርካሪው እስከ 400 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጉዞ እንደሚያደርግ፣ የአሠራር ወጪን በ88 በመቶ እንደሚቀንስ፣ ዜሮ የጭስ ልቀት እንደሚያስመዘግብ እና የፕሮጀክቱ ወጪ ከ4 እስከ 5 ዓመታት ውስጥ ሊመለስ እንደሚችል ተገልጿል።
በፕሮጀክቱ ፦
👉 70 ኪሎዋት PMSM ኤሌክትሪክ ሞተር፣
👉 65 ኪሎዋት ሰዓት ሊቲየም-አዮን ባትሪ፣
👉 3.3 ኪሎዋት AC/DC ቻርጂንግ ስርዓት እና Regenerative Braking ቴክኖሎጂ መተግበሩ ተመላክቷል።
#afromekina
Loading content...
