26 የከተማ አውቶብሶች ሙሉ በሙሉ ወደ ጋዝ መቀየራቸውን የትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ
26 የከተማ አውቶብሶች ከናፍጣ ወደ ጋዝ ሙሉ በሙሉ መቀየራቸውን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።
የተሽከርካሪዎች በካይ ጋዝ ልቀት መጠን እና የቅነሳ ስልቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብር እየተከናወነ ሲሆን፣ በመድረኩም መንግሥት ለአረንጓዴ ልማት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እየሠራ ይገኛል ያሉት በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የትራንስፖርት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አስምሮም ብርሃኔ፤ በዚህም 26 አውቶብሶች ሙሉ በሙሉ ወደ ጋዝ መቀየራቸውን ተናግረዋል።
በተጨማሪም በመዲናዋ የአየር ብክለትን ለመቀነስ የከተማ አስተዳደሩ ስድስት መቶ የከተማ አውቶብሶችን መግዛቱን አስረድተዋል።
የትራንስፖርት ቢሮ በመዲናዋ የአየር ብክለትን ለመቀነስ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል ያሉት ኃላፊው፤ ከብክለት ነፃ የሆኑ የትራንስፖርት አገልግሎቶች በመዲናዋ እንዲስፋፉ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ጋዝ ማውጣት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎችን ወደ ጋዝ የመቀየር ሥራ መጀመሯ ይታወቃል።
#afromekina
Loading content...
