ሕገ-ወጥ የተሽከርካሪ ጥቁር ሽፋን በሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር መጀመሩን ፖሊስ ገለጸ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፣ ህገ ወጥ የይለፍ ወረቀት በሚጠቀሙ፣ ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ አካል ውጪ የሆነ የጥቁር ስቲከር ፈቃድ ወረቀት እንዲሁም በልየ ልዩ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች ውስጥ የተገኙ ሞተር ሳይክልና ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ዋና ጠቅላይ መምሪያው በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ ባደረገው ቁጥጥር አንድ ሺህ አንድ መቶ አስራ አንድ ተሽከርካሪዎች ላይ በደንቡ መሰረት ዕርምጃ መውሰዱን የትራፊክ ዋና መምሪያ ኃላፊው ኮማንደር አበራ ባይሳ ገልፀዋል፡፡
ኃላፊው አክለዉም ጊዜው ያለፈበትና ፈቃድ ሰጪው አካል የማይታወቅ የስቲከር ፈቃድ ወረቀት የያዙ 8 መቶ 99፣ 153 በተለያዩ የደንብ ጥሰቶች ውስጥ የተገኙ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች እንዲሁም አፈር ጭነው መንገድ ያበላሹ 59 ተሽከርካሪዎች ላይ በትራፊክ ደንቡ መሰረት ህጋዊ ዕርምጃ ተወስዷልም ብለዋል፡፡
#afromekina
Loading content...
