አዲስ የተሸከርካሪ ሰሌዳ መለያ ቁጥር (ታርጋ) መስጠት እንደሚጀምር ተገለፀ
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት ያለዉ አዲስ የታርጋ ለውጥ ለማድረግ ሲያከናውን የቆየውን የቅድመ ዝግጅት ስራ አጠናቆ በቅርቡ አዲስ የተሸከርካሪ ሰሌዳ መለያ ቁጥር (ታርጋ) መስጠት እንደሚጀምር አስታወቀ።
የታርጋ መስጠት ስራዉ ከመጀመሩ በፊት ግለሰቦች ወይም ተቋማት የሚፈልጓቸዉን የሰሌዳ ቁጥሮች አጫርቶ ላሸነፉ አካላት ለመስጠት እንደሚፈልግ ገልጿል።
የስርጭት ስራዉ ከመጀመሩ በፊት ግለሰቦች ወይም ተቋማት የሚፈልጉትን ቁጥር በመለየት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ 5ኛ ፎቅ በመቅረብ ከ17/07/18 ዓ/ም ጀምሮ ባለዉ አንድ ሳምንት ጊዜ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።
#afromekina
