ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት መጀመሯን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ!
ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እያደረገች ያለው ሽግግር ወደ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች (ገልባጮች) መሸጋገሩን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገለጸ።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መረጃ መሠረት፤ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች አሁን ላይ ወደ ሀገር ውስጥ እየገቡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቱ ቀደም ሲል የጀመረችውን የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽግግር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ገልጿል።
እንደ ሀገር የኤሌክትሪክ መኪኖች ብቻ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ የተጀመረው ሽግግር፣ አሁን ላይ አዲስ የፖሊሲ ለውጥ በመደረጉ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አመልክቷል። በዚህም መሠረት “በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች እና የኢንዱስትሪ መሣሪያዎች አሁን የእቅዱ አካል ናቸው” ሲል ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ መንግሥት የነዳጅ ወጪን ለመቀነስና የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲዎቹ ሳቢያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አጠቃቀም ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ሲገልጽ ሰንብቷል። አሁን የተጀመረው “ወደ ኤሌክትሪክ የሚሰሩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች” ሽግግርም የሎጂስቲክስ ዘርፉን ይበልጥ ዘመናዊና ወጪ ቆጣቢ እንደሚያደርገው ሚኒስቴሩ ገልጿል።
#afromekina
Loading content...
