የናፍጣ አቅርቦት በድጋሚ ወደ 9 ሚሊየን ሊትር ከፍ እንዲል መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤በመካከለኛው ምስራቅ በነበረው ጦርነት ምክንያት ተቀንሶ የነበረው የናፍጣ ነዳጅ አቅርቦት ወደ ቀድሞው መጠን እንዲመለስ መወሰኑን አስታውቀዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ቀደም ሲል በጦርነቱ ሳቢያ በቀን 9 ሚሊየን ሊትር የነበረው የናፍጣ አቅርቦት በግማሽ ቀንሶ 4.5 ሚሊየን ሊትር ብቻ እንዲቀርብ ተደርጎ ቆይቷል።
አሁን ላይ ግን መንግሥት ያለውን የምርትና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ አቅርቦቱ ወደ ነበረበት 9 ሚሊየን ሊትር እንዲመለስ ወስኗል።
ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ለነዳጅ ድጎማ የሚመደበው በጀት በወር የ20 ቢሊየን ብር ጭማሪ የታየበት ሲሆን፤ይህም አጠቃላይ የሀገሪቱን የነዳጅ ድጎማ ከ300 ቢሊየን ብር በላይ እንዲያደርሰው ተገልጿል።
የናፍጣ ማጓጓዝ ሥራው ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ዛሬ የተጀመረ ሲሆን፤ከነገ ጀምሮ ደግሞ ወደ ተለያዩ ክልሎች ስርጭት እንደሚደረግ ተጠቁሟል።
ይህ እርምጃ በሀገሪቱ ያለውን የትራንስፖርት እና የግብርና እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
#afromekina
Loading content...
