በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የህንድ ኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል በገበያ ላይ ዋለ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የህንድ ኤሌክትሪክ ሞተርሳይክል የሆነው ቢጋስ ምርት በኒያ የሀገር በቀል ድርጅት ለገበያ ቀረበ።
ከህንድ የሚገቡት እነዚህ ኤሌክትሪክ ሞተርሳይክሎች በኢትዮጵያ የሚገጣጠሙ ሲሆን ዋጋቸውም ለገበያው ተመጣጣኝ እንዲሆን መደረጉ ተጠቅሷል።ተሽከርካሪዎቹን ወደ ኢትዮጵያ ያስገባው ድርጅት ከዚህ በፊት የህንድ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ አፓቺ እና ቦክሰር የተሰኙ ሞተርሳይክሎችን በማስገባት በኢትዮጵያ ገበያ ተወዳጅነት አትርፏል።
አሁን ደግሞ ከገበያው ፍላጎት እና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የሚጣጣሙ ኤሌክትሪክ ሞተርሳይክሎችን ወደ ሀገሪቱ ማስገባቱን አስታውቋል።
ቢጋስ የተሰኙት የኤሌክትሪክ ሞተር ተሽከርካሪዎች እስከ 3 ሺህ 500 ዋት በላይ አቅም ያላቸው ኤሌክትሪክ ሞተሮች እንዳሏቸው ተገልጿል። ተሽከርካሪዎቹ በነዳጅ ከሚሰሩ ሞተርሳይክሎች በተለየ የድምፅ እና የአየር ብክለትን በመቀነስ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የሚጣጣም የመጓጓዣ አማራጭ እንደሚያቀርቡም ተጠቁሟል።
ከሞተርሳይክሎቹ ጋር ዘመናዊ የቴክኖሎጂና የሶፍትዌር ድጋፎችም መካተታቸው ተገልጿል። በጂፒኤስ ሲስተም የተሽከርካሪውን አቅጣጫና አቀማመጥ መከታተል፣ የብልሽት ሁኔታዎችን መለየት፣ የባትሪ ቻርጅ መጠንን እና የተጓዘውን ርቀት ማወቅ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ተካተውበታል።
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሞተር አጠቃቀም እየጨመረ በመምጣቱእንደዚህ ቢጋስ ያሉ አዳዲስ ምርቶች የከተማ ትራንስፖርትን ለማሻሻል፣ የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ እና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የሚጣጣም የመጓጓዣ አማራጭን ለማስፋፋት ያግዛሉ ተብሏል።
የኒያ ሞተርስ ባለቤት ኑሩ ሳክ አደም ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት የኤሌክትሪክ ሞተርሳይክሎቹ በአካባቢ ጥበቃ፣ በነዳጅ ወጪ ቅነሳ እና በዘመናዊ የትራንስፖርት አማራጭ ማስፋፋት ረገድ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ ብለዋል።
በቀጣይም በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎችን ወደ ገበያ ለማስገባት ዕቅድ መኖሩ ተገልጿል።
#afromekina
Loading content...
