በሞተር ብስክሌት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ።
ከነገ ጠዋት 12:00 ሠዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ ይቻላል።
በአዲስ አበባ ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም ፦
- ወንጀል የመፈፀም፣
- የተሰረቁ እቃዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወር፣
- የመንገድ ትራፊክ ህጎችን የመጣስ
• በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣
• ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣
• ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣
• የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም ወ.ዘ.ተ. በአሽከርካሪዎቹ በስፋት የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መሆናቸውን በመግለፅ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ማሽከርከር ተከልክሎ ነበር።
አሁን እገዳው መነሳቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አሳውቋል።
የሞተር ሳይከል መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያላቸውና መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያደሱ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ከነገ ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ/ም ጠዋት 12:00 ሠዓት ጀምሮ የትራንስፓርትና የትራፊክ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የወጡ ህጎችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዷል።
ፖሊስ ህግን የማስከበር ስልጣንና ኃላፊነቱን በመጠቀም ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ አሳስቧል።
ዋና ጠቅላይ መምሪያው የመንቀሳቀሻ ፈቃድ የሌላቸው እና ፈቃድ ሳያድሱ በሚንቀሳቀሱ የሞተር አሽከርካሪዎች ላይ በህግ አግባብ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።
#afromekina
Loading content...
