አየር መንገዱ ከሶስት አስርት ዓመታት በኋላ ሊመለስ ነው
ከሰላሳ ዓመታት በላይ አገልግሎት አቋርጦ የቆየው የሶማሊያ ብሔራዊ አየር መንገድ በቀጣዩ ወር በድጋሚ ሥራ ሊጀምር መዘጋጀቱ ተዘግቧል ።
ካፒታል ጋዜጣ እንዳስነበበው አየር መንገዱ በ 1991 በሀገሪቱ ከተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነት ጋር ተያይዞ መሥራት አቆመው ነበር።
አሁን ላይ በሁለት አዲስ የኤርባስ A320 አውሮፕላኖች አገልግሎቱን ለመጀመር እቅድ ተይዟል።
ይህ ድጋሚ መጀመር የሶማሊያን የአቪዬሽን ዘርፍ እንደገና ለመገንባት እና ከቀጠናዊ እንዲሁም ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ጋር ያለውን የአየር ትስስር ለማሻሻል ከሚደረጉ ሰፊ ጥረቶች አንዱ አካል መሆኑ ታውቋል።
#afromekina
Loading content...
