የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ከጀሞ ፒያሳ የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታን በልዩ ትኩረት እየከናወነ እንደሚገኝ ገለጸ
የአአዲስአበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ዳኛቸዉ ሽፈራዉ ከጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍላጎትና የአቅርቦት አለመመጣጠን ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ የጀሞ-ፒያሳ የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታን በልዩ ትኩረት እየከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ይህ 15 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የመንገድ ፕሮጀክት አውቶቡሶች ብቻ የሚጓዙበት የተለየ መስመር የሚኖረው ይሆናል ብለዋል።
ወደ አገልግሎት ሲገባ በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ የማጓጓዝ አቅም ስለሚኖረው፣ በአካባቢው የሚታየውን የታክሲ ሰልፍ በእጅጉ እንደሚያቃልል ይጠበቃል።
የትራንስፖርት ቢሮው እንደገለጸው፣ ፕሮጀክቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የክትትል ስርዓት የሚኖረው ሲሆን፣ አውቶቡሶቹ የሚመጡበትን ሰዓት ተሳፋሪዎች አስቀድመው እንዲያውቁ የሚያስችል አሰራርም ይኖረዋል ብለዋል።
ይህ የትራንስፖርት ስርዓት በሌሎች የከተማዋ ዋና ዋና መስመሮች ላይም ተሞክሮው እንዲሰፋ እቅድ ተይዞለታል ተብሏል።
#afromekina
Loading content...
