ቴስላ በሰማይ ላይ የሚበር አዲስ የመኪና ሞዴል አስተዋወቀ
ቴስላ ከስፔስ ኤክስ ጋር በመተባበር የቴክኖሎጂውን ዓለም የሚያስደንቅ አዲስ ተሽከርካሪ ይፋ አድርጓል። ከመሬት ተነስቶ በአየር ላይ የመገለባበጥ አቅም እንዳለው የተነገረለት ይህ የሮድስተር መኪና ሞዴል፣ የሮኬት ቴክኖሎጂን ከመኪና ጋር በማቀናጀት የሰዎችን የጉዞ መንገድ የሚቀይር አስደናቂ ፈጠራ ነው።
ይህ አዲሱ ተሽከርካሪ በመደበኛ መንገድ ላይ እንዲነዳ የማይፈቀድለት ሲሆን፣ የሚሰጠውም ለልዩ ፈቃድ ባለቤቶች ብቻ ነው። የፈጠራ ባለሙያዎችና የቴክኖሎጂ አፍቃሪዎች በጉጉት የሚጠብቁት ይህ ድንቅ ሞዴል፤ የሙከራ ግምገማዎችን አጠናቆ በፈረንጆቹ 2028 ለገበያ ለማብቃት ታቅዷል። ነገር ግን እስካሁን ዋጋው ይፋ አልተደረገም።
#afromekina
Loading content...
