በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያገረሸው ውጥረት የዓለም የነዳጅ ዋጋን ማናሩ ተገለጸ
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ውጥረት እንደገና በማንሰራራቱ ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ።
ዛሬ ጠዋት የወጡ ኢኮኖሚያዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል በሚደረገው የነዳጅ ጭነትና የባህር ትራንስፖርት ላይ መስተጓጎል ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት የነዳጅ ዋጋን ከፍ አድርጎታል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ የዋጋ መለኪያ የሆነው የብሬንት ነዳጅ የወደፊት ዋጋ በ1.4 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በአንድ በርሜል 98.5 ዶላር የደረሰ ሲሆን፤ይህም ባለፉት ስድስት ሳምንታት ውስጥ የተመዘገበ ከፍተኛው የዋጋ ደረጃ ሆኗል።
የነዳጅ ገበያ ተንታኞች እንደሚሉት፤በክልሉ ያለዉ አለመረጋጋት በፍጥነት የማይረግብ ከሆነ የነዳጅ ዋጋ በቅርብ ቀናት ውስጥ ተጨማሪ ጭማሪ ሊያሳይ ይችላል በሚል የነጋዴዎች ስጋት እየጨመረ ይገኛል።
#afromekina
Loading content...
