ታንዛኒያ ከ10 ዓመታት በኋላ አዲስ የተፈጥሮ ጋዝ አገኘች
ታንዛኒያ በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኘው የምናዚ ቤይ አካባቢ ከፍተኛ መጠን ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ማግኘቷን አስታወቀች። ይህ ግኝት ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያው ሲሆን፣ መጠኑም 6.3 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ይደርሳል።
አዲሱ የተፈጥሮ ጋዝ በሚቀጥለው ወር መጀመሪያ ላይ ምርት መስጠት የሚጀምር ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ የኃይል አቅርቦትን በጣም ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።
በአሁኑ ወቅት ታንዛኒያ 57.54 ትሪሊዮን ኪውቢክ ጫማ የሚደርስ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አላት። የተፈጥሮ ጋዝ የሀገሪቱን 80% የኃይል ፍላጎት የሚሸፍን በመሆኑ፣ አዲሱ ግኝት የፋብሪካዎችንና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ዕድገት ለማፋጠን ይረዳል።
በተጨማሪም ሀገሪቱ በተመጣጣኝ ዋጋ ንፁህና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንድታገኝ ትልቅ አስተዋፅዖ ያደርጋል።
#afromekina
Loading content...
