ደቡብ ሱዳን አዲስ ግዙፍ የነዳጅ ክምችት አገኘች
ደቡብ ሱዳን በፓሎች የነዳጅ ማውጫ ቀጠና (ብሎክ 3 እና 7) ውስጥ በሚገኘው አል-ናህላ በተባለው ስፍራ ሌላ አዲስ የነዳጅ ክምችት አግኝታለች፤ ይህም ለአገሪቱ የኢነርጂ ዘርፍ ትልቅ ተስፋን የሰነቀ መልካም እድገት መሆኑ ተገልጿል።
በአካባቢው ከሚገኙት የነዳጅ ጉድጓዶች መካከል አንዱ በአሁኑ ወቅት በቀን ወደ 5,440 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ እያመረተ የሚገኝ ሲሆን፥ ይህ አዲሱ ግኝት ደግሞ በአሁኑ ወቅት በቀን 100,000 በርሜል ገደማ የሆነውን የአገሪቱን አጠቃላይ የነዳጅ ምርት ይበልጥ ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል።
#afromekina
Loading content...
