ደቡብ_ኮሪያዊው የሞተር አምራች ኩባንያ ኬጂኤም በ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሊገነባ ነው
ይህም ምርቶቹን ለ ምስራቅ_አፍሪካ ገበያዎች ለማቅረብ ታሳቢ ያደረገ ነው
ደቡብ ኮሪያዊው የሞተር ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ኬጂ ሞቢሊቲ (#KGM) በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (#EV) መገጣጠሚያ ፋብሪካ ለመገንባት መዘጋጀቱንና በፈረንጆቹ 2027 የመጀመሪያ አጋማሽ ማምረት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና ተሽከርካሪዎቹ ወደ ተለያዩ የምሥራቅ አፍሪካ ገበያዎች እንደሚላኩ ሴኦል ኢኮኖሚክ ዴይሊ በዛሬው እለት ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ፣ ኬጂኤም የመገጣጠም ሥራውን ለማቋቋም በትናትናው እለት ከኢትዮጵያው ቢኤንድሲ ማኑፋክቸሪንግ ግሩፕ እና ከየንግሳን ግሎኔት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
ግንባታው በጥቅምት ወር ለመጀመር የታቀደ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ዓመታዊ የምርት መጠን የኬጂኤም ቶሬስ ኢቪኤክስ (Torres EVX) እና ሙሶ ኢቪ (Musso EV) ሞዴሎችን ጨምሮ ወደ 1 ሺህ ገደማ ተሽከርካሪዎች ይሆናል ተብሎ ተገምቷል።
በስምምነቱ መሠረት፣ ቢኤንድሲ የፋብሪካውን ቦታ እና መሠረተ ልማት በማመቻቸት ግንባታውን የሚቆጣጠር ሲሆን፣ የንግሳን ግሎኔት ደግሞ የፋብሪካ ዲዛይን፣ ኢንጂነሪንግ እና ቴክኒካል ድጋፍ እንዲሁም የማምረቻ መሣሪያዎችን ያቀርባል። ኬጂኤም ለአገር ውስጥ መገጣጠሚያ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን እና እቃዎችን ያቀርባል።
#afromekina
Loading content...
