ሩሲያ ነዳጇን ዳግም ወደ ቀድሞ ደንበኞቿ መላክ መጀመሯ ተገለጸ
ሩሲያ በናፍጣ ነዳጅ ኤክስፖርት ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ ማንሳቷን ተከትሎ፣ ነዳጇን ዳግም ወደ ቀድሞ ደንበኞቿ መላክ መጀመሯ ተገለጸ
የዓለም አቀፍ የመርከብ እንቅስቃሴ መከታተያ መረጃዎች እንዳመለከቱት፤ ሩሲያ በናፍጣ ነዳጅ ኤክስፖርት ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ ካነሳች በኋላ የነዳጅ ጭነቶቿ ወደ ቀድሞ ዋና ዋና ደንበኞቿ መመለስ ጀምረዋል።
እንደ ኬፕለር (Kpler) እና ኤል.ኤስ.ኢ.ጂ (LSEG) የትራንስፖርት መረጃዎች ከሆነ፤ ከቅርብ ቀናት ወዲህ ቢያንስ ሁለት ግዙፍ የሩሲያ የናፍጣ ጫኝ መርከቦች ወደ ቱርክ እና ብራዚል ጉዞ መጀመራቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች ተመዝግበዋል።
የሞስኮ የናፍጣ ኤክስፖርት እገዳ መነሳት የተቻለው በአሜሪካ አደራዳሪነት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም በዓለም አቀፉ የነዳጅ ገበያ ላይ የተፈጠረውን ጫና ያቃልላል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዩናይትድ ስቴትስ በመቀጠል በዓለማችን ሁለተኛዋ ትልቅ የናፍጣ ነዳጅ ላኪ የሆነችው ሩሲያ፤ በነዳጅ ማጣሪያዎቿ ላይ በዩክሬን በኩል ይሰነዘርባት ከነበረው ተደጋጋሚ ጥቃት ጋር በተያያዘ የውጭ አቅርቦቷን ቀንሳ የቆየች ሲሆን፣ በመቀጠልም ነዳጅ ወደ ውጭ እንዳይወጣ እገዳ ጥላ ቆይታ ነበር።
#afromekina
Loading content...
