ያለ መሪ እና ፔዳል የሚሰራው የሮቦት ታክሲ አገልግሎት በይፋ ጀመረ
የኤሎን መስክ ኩባንያ የሆነው ቴስላ, በዘመናዊ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተውን ሙሉ በሙሉ በራስ ሰር (Driverless) የሚንቀሳቀሰውን “ሳይበር ካብ” (Cybercab) የተሰኘውን የሮቦት ታክሲ አገልግሎት በአሜሪካ (ቴክሳስ ኦስቲን) በይፋ ሥራ አስጀምሯል።
ዲዛይን እና አሰራር፡ ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) እና ካሜራዎች ብቻ የሚመራ ሲሆን፣ የመሪ መሽከርከሪያ (Steering Wheel) ወይም የፍሬን/አክሰለሬተር ፔዳሎች የሉትም።
ምቾት እና አገልግሎት፡ ለሁለት ተሳፋሪዎች ብቻ የተነደፈ ሲሆን፣ ውስጡ እንደ ሰፊ መዝናኛ ላውንጅ የተዘጋጀ ግዙፍ የክትትል ስክሪን እና እጅግ ዘመናዊ የድምፅ አቀንቃኝ ተካትቶለታል። ተሳፋሪዎች በልዩ የሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት ታክሲውን ጠርተው መጠቀም ተጀምረዋል።
የወደፊት ዕቅድ፡ ኤሎን መስክ የዚህ ተሽከርካሪ የሽያጭ ዋጋ ወደፊት ከ30,000 ዶላር በታች እንደሚሆን ገልፆዋል።
#afromekina
Loading content...
