የነዳጅ ኮንትሮባንድን መከላከል የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማስከበር ጉዳይ ነው፡- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ያለው ጦርነትና የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት በዓለም አቀፉ የነዳጅ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል መፍጠሩን የጠቀሰው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፤ በዚህም ምክንያት በበርካታ ሀገራት የማደያዎች መዘጋትና ማኅበራዊ ቀውሶች እየተባባሱ እንደሚገኙ አመላክቷል።
ኢትዮጵያ ይህንን ከባድ ፈተና በተወሰነ ደረጃም ቢሆን መቋቋም የቻለችው መንግሥት ላለፉት ስምንት ዓመታት በውኃ፣ በነፋስ፣ በፀሐይ እና በጂኦተርማል የታዳሽ ኃይል ልማት ላይ ባከናወናቸው ግዙፍ ስትራቴጂያዊ ፕሮጀክቶች መሆኑንም አገልግሎቱ ገልጿል።
በተለይም የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የተለያዩ የኃይል አማራጮች እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ንቅናቄ ዛሬ የሀገራችንን የሕልውና ዋስትና መሆናቸውን ተጠቅሷል።
#afromekina
Loading content...
