ፊሊፒንስ በነዳጅ እጥረት የተነሳ ተጨማሪ የሩሲያን ነዳጅ ዘይት ለመግዛት የአሜሪካን ፈቃድ ጠየቀች
ፊሊፒንስ ተጨማሪ የሩስያን ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ለመግዛት የአሜሪካን ፍቃድ እየፈለገች ሲሆን ከውጭ ሀገር ምርቱን በማስመጣት ላይ የተመሰረተችው ፊሊፒንስ እየነዳጅ አቅርቦቶችን ለማጠራቀም እየጣረች ትገኛለች፡፡ምንም እንኳን የአሜሪካ ምላሽ ባይኖርም፣ “በጣም አዎንታዊ ምለሽ እየጠብቅን ነዉ” ሲሉ የኢነርጂ ፀሐፊ ሻሮን ጋሪ ተናግረዋል።
"ይህም ካልተሳካ ሌሎች አማራጮችም አሉን" ሲሉ አክለዋል፡፡የዩናይትድ ስቴትስ እና የእስራኤል ጦርነት በኢራን ላይ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቢያንስ አራት ሚሊዮን በርሚል ጭነቶች ከተሰረዙ በኋላ የሀገሪቱ ብቸኛ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ባለፈው ወር ወደ 2.5 ሚሊዮን በርሜል ማግኘቱ ይታወሳል።ዋሽንግተን ባለፈው ወር በሩሲያ ላይ ከዩክሬን ጦርነት ጋር የተቆራኙትን አንዳንድ ማዕቀቦች በማቃለል እስከ ኤፕሪል 11 ድረስ በባህር ላይ ያለውን የሩሲያ ዘይት እንዲገዙ ለመፍቀድ የሆርሙዝ የባህር ዳርቻ ከተዘጋ በኋላ የኃይል ገበያዎችን ለማረጋጋት ሞክሯል፡፡
በሌላ መረጃ ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል በኢራን ላይ በከፈቱት ጦርነት የተነሳ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ለማቃለል በማለም በሩሲያ ላይ የተጣለዉን የማዕቀብ እፎይታ በመቃለሉ ሞስኮ በመጋቢት ወር ላይ ከነዳጅ የምታገኘዉ ገቢ በእጥፍ ጨምሯል።
ባለፈው ወር ወደ ውጭ የሚላከው ድፍድፍ ወደ 7.1 ሚሊዮን በርሜል ሲደርስ በየካቲት ወር ከነበረው 320 ሺ በርሜለ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡ በዚህም ሀገሪቱ 19 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች፡፡ አሜሪካ የሩስያ ድፍድፍ ሽያጭ ላይ አንዳንድ ገደቦችን በማንሳቷ ሀገራት እስከ ኤፕሪል 11 ድረስ በባህር ላይ ያለዉን ነዳጅ ዘይት እንዲገዙ አስችሏቸዋል።
#afromekina
Loading content...
