የኦላ ኤነርጂ እና ቶታል ኢትዮጵያ ውህደት የሞኖፖሊ ስጋት በመደቀኑ ተገታ
ኦላ ኤነርጂ የቶታል ኤነርጂ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያን ሀብትና ንብረት ሙሉ በሙሉ ለመግዛት ያደረገው ስምምነት፣ በንግድ ውድድርና ደንበኞች ጥበቃ ባለስልጣን ጊዜያዊ እግድ ተጣለበት።
ባለስልጣኑ ውህደቱ የነዳጅ ማሰራጨት ገበያውን ወደ 50 በመቶ ገደማ ለአንድ ኩባንያ አሳልፎ እንደሚሰጥና ይህም የገበያ የበላይነት (Monopoly) በመፍጠር በነዳጅ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ስጋት ይፈጥራል ማለቱን ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ቶታል ኤነርጂ ከ70 ዓመታት በላይ የቆየበትን የኢትዮጵያ ገበያ ለቀቅ ለማድረግ ከኦላ ኤነርጂ ጋር በፓሪስ ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል።
ስምምነቱ ከ120 በላይ የነዳጅ ማደያዎችን፣ የዱከም ማከማቻ ዲፖን እና የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የአቪዬሽን ነዳጅ አቅርቦትን ያካተተ ነበር።
ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ ፔትሮሊየም እና ኤነርጂ ባለስልጣን ይፋዊ ማመልከቻ እንዳልደረሰውና ውህደቱ ጥልቅ የህግ እና የውድድር ግምገማ እንደሚፈልግ አስታውቋል።
#afromekina
