በሳውዲ አረቢያ እና በባህረ ሰላጤው ግጭት የነዳጅ ዋጋ ከ2 በመቶ በላይ ማሻቀቡ ተገለጸ
በሳውዲ አረቢያ እና በባህረ ሰላጤው የተቀሰቀሱ አዳዲስ ግጭቶች የአቅርቦት ስጋትን በመፍጠራቸው የነዳጅ ዋጋ ከ2 በመቶ በላይ መጨመሩ ተገለጸ።
የብሬንት የነዳጅ ዋጋ በበርሜል 107 ዶላር ከ51 ሳንቲም የደረሰ ሲሆን፣ የአሜሪካው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዲየት የነዳጅ ዋጋም በበርሜል 102 ዶላር ከ32 ሳንቲም ደርሷል።
ይህ የዋጋ ጭማሪ ሊመጣ የቻለው ከኢራቅ በተነሳ የድሮን ጥቃት የሳውዲ አረቢያ የምዕራብ-ምሥራቅ የነዳጅ መስመር አርብ ዕለት መዘጋቱን ተከትሎ የአቅርቦት ሥጋት በመፈጠሩ መሆኑ ተመላክቷል።
ይህ ወሳኝ የቧንቧ መስመር የዓለምን የነዳጅ አቅርቦት እስከ 4 በመቶ ሊያስተጓጉል የሚችል አቅም ያለው ሲሆን፣ መስመሩ መዘጋቱን ተከትሎም በነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱ ታውቋል።
ቀጠናዊ ግጭቶችና በነዳጅ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች የዓለም አቀፍ የኢነርጂ ገበያን ፈተና ላይ መጣላቸው ተመላክቷል።
#afromekina
Loading content...
