በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ውጥረት በማገርሸቱ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ
ከሳምንታት አንጻራዊ ሰላም በኋላ፤ በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል የተጀመረው አዲስ ወታደራዊ ፍጥጫ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ስጋት ዳግም ቀስቅሶታል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ኢራን በድርጊቷ የምትቀጥል ከሆነ ‹‹በከባድ ሁኔታ›› እንደሚያጠቋት መዛታቸውን ተከትሎ፤በዛሬው ዕለት በዓለም አቀፍ ገበያ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።
ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ፍጥጫ እና የቃላት ምልልስ፤ሁኔታው ወደ ሰፊ ቀጣናዊ ጦርነት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት በኢንቨስተሮች ዘንድ እንዲፈጠር አድርጓል።
በዚህም ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ዛሬም ጭማሪው ቀጥሏል፡፡
የነዳጅ ገበያ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ፤በመካከለኛው ምስራቅ ያለው አለመረጋጋት በቀጠለ ቁጥር የነዳጅ አቅርቦት ላይ መስተጓጎል ሊፈጠር ይችላል የሚለው ስጋት የዋጋ ግሽበትን ሊያባብሰው ይችላል።
#afromekina
Loading content...
