ኒያላ ሞተርስ የ JMEB የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አስታዋወቀ
ኒያላ ሞተርስ አራት አይነት የJMEB ኦቶሞቢል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ አስገብቷል።
በቻይና ከሚገኙ ግዙፍ የመኪና አምራቾች በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጠው JMEB የመኪና አምራች ኩባንያ ከኒያላ ሞተርስ ጋር ባደረጉት ስምምነት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኢትዮጲያ ማስመጣት ጀምረዋል።
የኒያላ ሞተርስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ቦጋለ ይህ ስምምነት እንዲሳካ ትብብር ላደረጉ አካላት ምስጋና ያቀረብ ሲሆን በተለይ ሼክ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን አመስግነዋል።
የ JMEB ም/ክ ዳሬክተር ሚስተር ፍራንክ ው እንደተናገሩት ኩባንያው አራት አይነት አማራጮችን ይዞ ወደ ኢትዮጲያ ገበያ መቀላቀሉ ለሀገሪቱ የአውቶሞቲቭ ገበያ ትልቅ እድል መሆኑን አስታውቀዋል።
እነዚህ ተሽካሪዎች ከ 220 እስከ 550 ኪ/ሜትር መጓዝ የሚችሉ ሲሆን ባትሪያቸው እሰከ 8 ዓመት ጋራንቲ ወይንም ዋስትና የሚኖራቸው ሲሆን ቦዲያቸው ደግሞ እስከ ሶስት ዓመት የሚቆይ ዋስትና ይኖራቸዋል ተብሏል።
የኒሳን ኩባንያ አጋር የሆነው ኒያላ ሞተርስ ባለፉት 50 ዓመታት በአውቶሞቲቭ ዘርፍ ትልቅ ስራን እየሰራ ይገኛል።
ኒያላ ሞተርስ አዲስ አበባ ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤቱ ባለፈ በመቀሌ፣ በባህርዳር ፣ በሃዋስ፣በድሬዳዋና በጂማ ከተሞች ቅርንጫፎች አሉት።
#afromekina
Loading content...
