ለአሽከርካሪዎች የተሠጠ ማሳሰቢያ !
🛑 አምባጓሮ መፍጠር፦ ድርጊቱ የትራፊክ ደንብ መጣስንና መንገድ ላይ ጠብ (አምባጓሮ) ማንሳትን በአንድነት ያካተተ ከሆነ፣ ግለሰቡ (አሽከርካሪው):-
⚠️በ1996ቱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ መሰረት አንቀጽ 572 እና በ577 መሰረት ከ3 ወር እስከ 3 ዓመት እስራትና በትራፊክ ደንብም በተደራራቢነት ሊቀጣ ይችላል።
🛑የመንግሥት ሠራተኛ (የትራፊክ ፖሊስ/ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያ) የመንጃ ፈቃድ፣ የተሽከርካሪ መታወቂያ (ሊብሬ) ወይም ሌላ የሚፈለጉ መረጃዎችን አልሰጥም ወይም አላሳይም በማለት ሥራውን እንዳይሠራ በኃይል በማስገደድ ለመጠቀም በመዛት ከሞከረ:_
⚠️ጉዳዩ ወደ ከባድ ወንጀል ተቀይሮ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 441 መሠረት ከ3 ዓመት እስከ 5 ዓመት ጽኑ እስራት ልያስቀጣ ይችላል።
ህግን ማክበር የፍርሃት ሳይሆን *የስልጣኔ* እና *የኃላፊነት ስሜት* መገለጫ መሆኑን ተረድተን፣ ለህግ እና ህግን ለማስከበር ለቆሙ አካላት ተገቢውን ክብር መስጠት የሁላችንም የማይደራደር ግዴታ ነው።
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን!
#afromekina
Loading content...
