ኒጀር የ1.9 ቢ. ዶላር የነዳጅ ማጣሪያ ስምምነት ተፈራረመች
ኒጀር በዶሶ ከተማ በቀን 100 ሺህ በርሜል ነዳጅ የሚያጣራ ግዙፍ ፋብሪካ ለመገንባት የ1.9 ቢሊዮን ዶላር ውል ተፈራረመች።
ይህ አዲስ ፋብሪካ ሀገሪቱ አሁን ካላት የዚንደር ነዳጅ ማጣሪያ በአምስት እጥፍ ይበልጣል።
ፕሮጀክቱ ሀገሪቱ የራሷን ድፍድፍ ነዳጅ እንድታጣራ፣ ከውጭ ነዳጅ የመግዛት ጥገኝነቷን እንድትቀንስና ለአካባቢው ሀገራትም ነዳጅ እንድታቀርብ ይረዳታል።
ይህ ስምምነት ኒጀር በኃይል ዘርፍ በራሷ ለመቆምና የኢንዱስትሪ እድገቷን ለማፋጠን ለምታደርገው ጥረት ትልቅ እርምጃ ነው።
#afromekina
Loading content...
