ነዳጅ አቅራቢ ሀገራት ምርቱን ማቅረብ ማቆማቸውን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገለፁ‼️
ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር የነበራት የረጅም ጊዜ የነዳጅ ግብይት ውል በጦርነቱ ምክንያት መስተጓጎሉንና አቅራቢ ሀገራቱ ምርቱን ማቅረብ እንደማይችሉ ማሳወቃቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልጸዋል ።
በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትና ዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችሉ ውሳኔዎች መተላለፋቸውን አሳውቀዋል።
የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን የሚከታተል፣ ርምጃ የሚወስድና የነዳጅ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ዘርፍች የሚለይ ልዩ ክፍል መቋቋሙንም ይፋ አድርገዋል።
ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ጋር የነበራት የረጅም ጊዜ የነዳጅ ግብይት ውል በጦርነቱ ምክንያት መስተጓጎሉን ገልጸዋል።
አቅራቢ ሀገራቱ ምርቱን ማቅረብ እንደማይችሉ ማሳወቃቸውን አመልክተዋል።
በዚህም ምክንያት በግዥ ሂደት ላይ የነበረ ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ አለመቅረቡን ጠቅሰዋል።
በጦርነቱና አለመረጋጋቱ ምክንያት በነጭ ናፍጣ ላይ የነበረው የቀን አቅርቦት ከ9 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4 ነጥብብ 5 ሚሊዮን ሊትር ዝቅ ማለቱን ተናግረዋል።
ያጋጠመው የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ለመቋቋም ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የቅድሚያ አሰጣጥ ውሳኔ መተላለፉን ይፋ አድርገዋል።
በዚህም ፦
1. ነዳጅ የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች በማደያ የቅድሚያ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው
2. ከፍተኛ አምራችና የኤክስፖርት ድርጅቶች በቀጥታ፣
3. ልዩ ትኩረት የሚሹ የመንግሥትና የግል ፕሮጀክቶች በቀጥታ፣
4. የገቢና ወጪ ንግድን ጨምሮ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች፣
5. ግብርናን የሚያዘምኑ ትራክተሮች፣
6. የከተማና ሀገር አቀፍ የብዙሃን ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች
7. በናፍጣ የሚሰሩ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ነዳጅን በቅድሚያ እንዲያገኙ ተብሏል።
ከዚህ ውጭ የሚደረግ የነዳጅ ስርጭት ተገቢ ባለመሆኑ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ህብረተሰቡ ፦
1) ነዳጅን በቁጠባ እንዲጠቀም
2) የታዳሽ ኃይል አማራጮችን የመጠቀም ስልትን እንዲከተል
3) የእግር ጉዞ ባህልን እንዲያጎለብት
4) አላስፈላጊ የጉዞ ፕሮግራሞችን እንዲሰርዝና እንዲቆም
5) የሕዝብ ትራንስፖርትን እንዲጠቀም
6) በነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ተግባራትን እንዲያጋልጥ፤ ከመንግሥት ጋርም ተባብሮ እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል።
#afromekina
Loading content...
