⚠️ ለአሽከርካሪዎች የተላለፈ መልዕክት፡
የቢጫ ሳጥን ምልክት (Yellow Box Junction) ምንድነው? እንዴትስ እንጠቀምበት?
በቅርቡ በከተማችን መንገዶች ላይ ተግባራዊ መሆን ስለጀመረው የቢጫ ሳጥን ምልክት (Yellow Box Junction) ምን ያህል ያውቃሉ?
ይህ ምልክት በመጋጠሚያዎች ላይ የሚሳል፣ የተያያዙ መስመሮች ያሉት ቢጫ ሳጥን ሲሆን፣ ዋና ዓላማው የመንገድ መጋጠሚያዎች ሁልጊዜም ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ እና የትራፊክ መጨናነቅን መከላከል ነው።
🎯 የቢጫ ሳጥን ምልክት ጥቅሞች፡
📍መንገድ እንዳይዘጋ ይረዳል፦ መጋጠሚያዎች በማናቸውም ሰዓት ክፍት ሆነው እንዲቆዩ ያደርጋል።
📍የትራፊክ ፍሰትን ያሻሽላል፦ አቋራጭ መንገድ ለሚጠቀሙና ለድንገተኛ አደጋ ተሽከርካሪዎች (አምቡላንስና እሳት አደጋ) ፈጣን መተላለፊያ ይሰጣል።
📍አደጋን ይከላከላል፦ በመጋጠሚያዎች ላይ የሚከሰቱ የተሽከርካሪዎች መጋጨት አደጋዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።
🛑 ዋናውና ወሳኙ ህግ (አሽከርካሪዎች ሊያውቁት የሚገባ!)፦
"ከፊትዎ ያለው መንገድ ሙሉ በሙሉ ክፍት ካልሆነና ሳጥኑን ሳያቋርጡ መቆም የሚኖርብዎት ከሆነ፣ በፍጹም ወደ ቢጫው ሳጥን ውስጥ አይግቡ!"
መቼ መግባት ይቻላል? ከሳጥኑ ማዶ ያለው መንገድ ክፍት መሆኑንና ሳይቆሙ በቀጥታ ማለፍ የሚችሉ መሆንዎን እርግጠኛ ሲሆኑ ብቻ።
መቼ መግባት የተከለከለ ነው? ከሳጥኑ ባሻገር ያለው መንገድ በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ዝግ ከሆነ፣ አረንጓዴ መብራት ቢበራልዎት እንኳ ሳጥኑ ውስጥ ገብቶ መቆም በጥብቅ የተከለከለ ነው!
💡 ውድ አሽከርካሪዎች፦ ይህንን የትራፊክ ምልክት በወጉ በመገንዘብ፣ ደንቡን አክብረን በማሽከርከር እና መረጃውን ለሌሎች በማጋራት የበኩላችንን እንወጣ። ራሳችንንም ካላስፈላጊ የደንብ መተላለፍ ቅጣት እንጠብቅ!
#afromekina
Loading content...
