ሊቢያ በቀን 50 ሚሊዮን ኪዩቢክ ጫማ ጋዝ የማምረት አቅም ያለውን የጋዝ መስክ ሥራ አስጀመረች
በምሥራቅ ሊቢያ በየባሕር ዳርቻ ከተማዋ ብሬጋ የሚገኘው የአል-ረሻድ የተፈጥሮ ጋዝ መስክ ሥራ መጀመሩን የሊቢያ ብሔራዊ የነዳጅ ኮርፖሬሽን አስታውቋል።
አዲሱ የጋዝ መስክ ለኤሌክትሪክ ማመንጫ ማዕከላትና ለኢንዱስትሪ ዘርፎች የሚቀርበውን የጋዝ አቅርቦት እንደሚያሳድግ ተገልጿል።
ℹ️ ሊቢያ በቀን 2.4 ቢሊዮን ኪዩቢክ ጫማ ያህል የተፈጥሮ ጋዝ ታመርታለች። የተረጋገጡ የጋዝ ክምችቶቿ ከ53 እስከ 80 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ እንደሚደርሱ ይገመታል።
ሀገሪቱ በቧንቧ መስመሮች የተፈጥሮ ጋዝ ወደ አውሮፓ የምትልክ ሲሆን በሀገር ውስጥም ለኤሌክትሪክ ማመንጫና ለኢንዱስትሪ ዘርፎች ትጠቀምበታለች።
#afromekina
Loading content...
