የብሬንት የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ
በመካከለኛው ምስራቅ እየተስተዋለ የሚገኘው ጂኦፖለቲካዊ ውጥረት ለነዳጅ ዋጋ መናር መንስኤ ሲሆን፤ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ የ1.14 በመቶ ጭማሪ አድርጎ በአሁኑ ሰአት አንድ በርሜል በ 1መቶ14 ዶላር እየተሸጠ ይገኛል።
በሳዑዲ እየጨመረ የመጣው ጥቃት ለዚህ የዋጋ መናር ሌላኛዉ የሚነሳ ምክንያት ሆኗል።
የየመኑ ሁቲ አማጺቡድን በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ የቀይባህር ወደብ በያንቡ እና በነዳጅ ማጣሪያዎች እና በአየር ማረፊያ ላይ ላነጣጠረው ጥቃት ኃላፊነት ወስዷል።
በተጨማሪም አሜሪካ እና እስራኤል የኢራን የኢነርጂ መሰረተ ልማቶች ላይ ከመጪው የአሜሪካ የአጋማሽ ምርጫ በኃላ ጥቃት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ዘገባዎች ያሳያሉ።
ምንም እንኳን በቀጣናው ያለው ውጥረት እያየለ በመምጣቱ በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚደረገው የመርከብ ትራንስፖርት ላይ ስጋቶች ቢስተዋሉም፤ የገልፍ ሀገራት የድፍድፍ ነዳጅ ኤክስፖርት ከጦርነቱ በፊት ወደነበረበት እየተመለሰ ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል የአዉሮፓ የተፈጥሮ ጋዝ የአቅርቦት እጥረት ገጥሞታል ተብሏል፡፡
ከመካከለኛው ምስራቅ የሚላከው የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ጭነት መጠን ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ80 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል የተባለ ሲሆን፤ይህም የአውሮፓና የእስያ ገዢዎች ከፍተኛ ፉክክር እንዲያደርጉ ተፅዕኖ አሳድሯል።
በአሁኑ ወቅት የአውሮፓ የጋዝ ክምችት 74.62 በመቶ ሲሆን፤ ከ2009 ወዲህ የተመዘገበ ዝቅተኛው መጠን ነው።
#afromekina
Loading content...
