30 የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በ2019 በጀት ዓመት 30 የሆኑ የመንገድ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ለማስመረቅ አቅዶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በአስተዳደሩ የኮሙዩኒኬሽን ቡድን መሪ ዶክተር አስራት አሳሌ የቅድመ ዝግጅት እና ግንባታ ከሚደረግባቸው 30 ፕሮጀክቶች 21ዱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
ግንባታቸው ተጠናቆ የሚመረቁትና ለአገልግሎት ክፍት የሚሆኑት እነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ በመሆናቸው በክልሎች መካከል ያለውን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ትስስር ያጠናክራል ሲሉ ገልፀዋል።
የፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅ የህዝብና የእቃ ማጓጓዝ አገልግሎቱን ከማፋጠን ባለፈ፣የትራፊክ ፍሰቱን መጨናነቅ እንደሚያቀለው ተናግረዋል።
የመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታ የሀገሪቱን የንግድ እንቅስቃሴ ለማፋጠን፣ የአግሮ-ኢንዱስትሪ ምርቶችን ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እና የዜጎችን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ለማቃለል ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
በዚህም መሰረት አስተዳደሩ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው የጥራት ደረጃ እና የጊዜ ገደብ አጠናቆ ለህዝብ አገልግሎት ለማብቃት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በአጠቃላይ ለመሰረት ልማት ግንባታ 135 .7 ቢሊዮን ብር በመደብ በአዲሱ በጀት ዓመቱ ወደ ስራ መግባቱን ማስታወቁ ይታወሳል።
#afromekina
Loading content...
