በአዲስ አበባ ከተማ ከ1 ሺህ 300 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራን ለማከናወን ታቅዷል ።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2019 በጀት ዓመት ከ1 ሺህ 300 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ የተለያዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎችን ለማከናወን እቅድ መያዙን አስታውቋል።
የባለሥልጣኑ ምክትል ኃላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ ከሚከናወኑ የግንባታ ሥራዎች መካከል 60 ኪሎ ሜትር የአስፋልት፣ 63 ኪሎ ሜትር የኮብል ንጣፍ፣ 46.8 ኪሎ ሜትር የጠጠር እና 87.2 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ መልሶ ግንባታ ይገኙበታል ።
በተጨማሪም 21 ኪሎ ሜትር የፔዳል ሳይክል መተላለፊያ መንገድ እንዲሁም 14 የድልድይ የድጋፍ ግንብና የከልቨርት ግንባታ ሥራዎችም በዕቅዱ ተካትተዋል።
በመንገድ ጥገና በኩል ደግሞ 130 ኪሎ ሜትር የአስፋልት፣ 30 ኪሎ ሜትር የጠጠር እና 54 ኪሎ ሜትር የኮብል መንገድ ጥገና ይከናወናል ተብሏል።
እንዲሁም 508 ኪሎ ሜትር የድሬኔጅ መስመር ጽዳትና ጥገና፣ 325 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መከላከያ አጥርና የከርቭ ስቶን ቀለም ቅብን ጨምሮ ሌሎች የመንገድ መሠረተ ልማት ጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ታቅዷል።
ከግንባታና ጥገና ሥራዎች ጎን ለጎን የከተማዋ የመንገድ ኔትወርክ ደህንነቱ ተጠብቆ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ የመንገድ ሀብት ቁጥጥር፣ ክትትልና የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችም ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንደሚከናወኑ ተገልጿል።
#afromekina
Loading content...
