አዲሱ የበካይ ጋዝ ልቀት መቀነሻ ቴክኖሎጂ ነዳጅን 20 በመቶ እንደሚቀንስ ተገለጸ፡፡
በሎጂስቲክ ሚኒስቴር የትራንስፖርት አገልግሎትና ቁጥጥር ዘርፍ አማካሪ አቶ አሰፋ ሃዲስ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው አዲሱ የበካይ ልቀት መቀነሻ ቴክኖሎጂ የነዳጅ ፍጆታን 20 በመቶ እንደሚቀንስ ተናግረዋል።
ይህ ማለት 100 ሊትር ይሞላ የነበረው ተሽከርካሪ በ80 ሊትር እንዲጠቀም የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።
ቴክኖሎጂው ነዳጅ በየቀኑ ለሚሞላ ተሽከርካሪ ወጭውን እንድቀንስ የሚያደርግ በመሆኑ ግንዛቤው ላይ መሰራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
ቴክኖሎጂው የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በመንግስት በከሉል የታቀደ መሆኑን አንስተው የሚገጠመው ቴክኖሎጂ ነዳጁ በጣም እንዲቀጣጠል በማድረግ ታምቆ የሚወጣው ጭስ ወደ ሀይል እንዲቀይረው የሚያደርግ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ይህንን ቴክኖሎጂ ሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እና ያለውን ጥቅም ለማማሳወቅ ግንዛቤው ላይ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የመንግስት ተሽከርካሪዎች እንዲጠቀሙ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ጠቅሰዋል፡፡
#afromekina
Loading content...
