ሩሲያ ለአሜሪካ እና ለዓለም ገበያ ከፍተኛ መጠን ያለው ናፍጣ ልታቀርብ መሆኑ ተገለጸ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በስልክ ባደረጉት ውይይት፣ ሩሲያ ለአሜሪካ አስቸኳይ የናፍጣ አቅርቦት እንድታደርግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደገለጹት፣ በስምምነቱ መሰረት ሩሲያ በአስቸኳይ ከ300 ሺህ ቶን በላይ ናፍጣ ለአሜሪካ ገበያ የምታቀርብ ሲሆን፤ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ ደግሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ተጨማሪ የናፍጣ አቅርቦት ይከተላል ተብሏል።
በሌላ በኩል፣ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከስልክ ውይይቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት፤ ይህ ወደ አሜሪካ እና ወደ ዓለም አቀፉ ገበያ የሚደረገው የናፍጣ አቅርቦት አጠቃላይ የዓለም ኢኮኖሚን የሚጠቅምና ገበያውን የሚያረጋጋ ነው ብለዋል።
ሁለቱ መሪዎች ያደረጉት ይህ ስምምነት በዓለም አቀፍ ደረጃ በነዳጅ ገበያ ላይ የሚታየውን ጫና እና የዋጋ መዋዠቅ ለማርገብ ጉልህ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
#afromekina
Loading content...
