የቀላል ባቡር እና አውቶቡስ የትራንስፖርት አገልግሎትን በአንድ የክፍያ ካርድ ለመስጠት የሚያስችል አሰራር ሊጀመር መሆኑ ተገለጸ፡፡
ተገልጋዮች የቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ተጠቅመው ሲወርዱ ተጨማሪ ገንዘብ ሳያስፈልጋቸው ወይም ሳይከፍሉ የአውቶቢስ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ እየተሰራ መሆኑ ተገልጻል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ደገፉ ገብረመድህን ቀላል ባቡር እና አውቶቢስ የትራንስፖርት አገልግሎት በአንድ የክፍያ ካርድ ተገልጋይዎችን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ የሚያስችል የተቀናጀ አሰራር ሊዘረጋ መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ቀላል ባቡር እና የከተማ አውቶብስ የብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ እንደመሆናቸው የከተማዋን እድገት የሚመጥን አሰራር መዘርጋት አለበት ብለዋል፡፡
አንድ ተገልጋይ ለባቡር ትራንስፖርት በያዘው ካርድ አውቶቢስ መጠቀም ሲችል በተመሳሳይ አውቶቢስ ለመጠቀም በያዘው ካርድ የባቡር ትራንስፖርት መጠቀም የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ይሄን የተቀናጀ የቴክኖሎጂ አሰራርን ለማስጀመር ዝግጅቶች እየተደረገ መሆኑን አንስተው የግብዓት የማሰባሰብ ስራው በአብዛኛው እየተጠናቀቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቀጣይ ባሉት 5 እና 6 ወራት ውስጥ ተቋሙ ወደ ዘመናዊው የተቀናጀ የቴክኖሎጂ አሰራር እንደሚሸጋገር የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ደገፉ ጠቁመዋል፡፡
በተለይም የክፍያ አሰባሰብ እና የካርድ አጠቃቀም አሰራሩ ከባቡር ጋር የተሳሰረ እንዲሆን በመደረጉ ተሳፋሪዎች በአንድ ካርድ ብቻ ባቡርም ሆነ የከተማ አውቶብስ መጠቀም እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡
#afromekina
Loading content...
