ባለሀብቶች ለትልቁ የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ጅማሮ 400 ሚሊዮን ዶላር ቃል ገቡ
🛢ትልቁን የአፍሪካ የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ የማምረት አቅም በቀን ከ700 ሺህ ወደ 1.4 ሚሊዮን በርሜል ለማሳደግ፤ ዳንጎቴ በመስከረም ወር ወይም አጋማሽ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያካሂደው ይፋዊ የአክሲዮን ሽያጭ እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ አቅዷል። ባለሀብቶች ከወዲሁ ከታለመው ገንዘብ ውስጥ 400 ሚሊዮን ዶላር ቃል እንደገቡ አንድ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
❗️ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት፦ ማጣሪያው የናይጄሪያን የሀገር ውስጥ የነዳጅ ፍላጎት ለማሟላት፣ የወጪ ንግድን ለማሳደግ እና በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ሳቢያ የተከሰተውን የቀጣናውን የአቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና አለው።
#afromekina
Loading content...
