የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ያለውን አጠቃላይ የነዳጅ ድጎማ እንዲያነሳ IMF መከረ።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ወደ ቀደመው መደበኛ ሁኔታ ሲመለስ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ወቅት እያደረገ ያለውን አጠቃላይ የነዳጅ ድጎማ እንዲያነሳ መከረ። በምትኩ መንግስት የነዳጅ ድጎማውን ሀብታም ደሃ ሳይል ለሁሉም ከማዳረስ ይልቅ፣ ድጋፍ ለሚገባቸው ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ እንዲያደርግ ተቋሙ አሳስቧል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር የዘንድሮውን የነዳጅ ድጎማ ጣሪያ በ20 ቢሊዮን ብር የገደበ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ያለበትን ከፍተኛ እዳ ለማቃለል እና የፋይናንስ አቅሙን ለማሳደግ የ286 ቢሊዮን ብር የካፒታል ማሳደጊያ በጀት አጽድቋል።
ከዓለም ባንክ (World Bank) - የተመደበው መጠን - 170 ቢሊዮን ብር
ከፌደራል መንግስት በጀት - የተመደበው መጠን - 116 ቢሊዮን ብር
አጠቃላይ ድምር = 286 ቢሊዮን ብር
ከገንዘብ ሚኒስቴር የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ መንግስት የነዳጅ ዋጋን በገበያ እንዲወሰን በማድረግ፣ ድጎማውን ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እና ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ በዲጂታል የክፍያ ስርዓት ለማድረግ አቅዷል። የዚህ ሽግግር አካል የሆነው የሴፍቲኔት (PSNP) ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ቁጥር በገጠር ከ8 ሚሊዮን ወደ 9.5 ሚሊዮን ከፍ የሚል ሲሆን፣ ለድንገተኛ አደጋ ምላሽ የሚሆን ተጨማሪ 4 ቢሊዮን ብርም ተመድቧል። በአንጻሩ የአውሮፕላን (Jet-fuel) ነዳጅ ድጎማ ሙሉ በሙሉ ተነስቷል።
ይህ አጠቃላይ ድጎማን የማንሳት እቅድ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በማሻቀቡ ለጊዜው ዘግይቶ የነበረ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ኃላፊዎች አስረድተዋል።
ምስል በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተሰራ
#afromekina
Loading content...
