በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ እና ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ነዳጅ በቁጥጥር ስር ዋለ
በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮቦልቻ ወረዳ በሕገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል ።
የአዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮቦልቻ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሐላፊ ኢንስፔክተር ቡሎ ዲንሣ እንደገለፁት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3/9961 ኢቲ ተሣቢ ተሽከርካሪ በድርጊቱ ተሳትፋል።
ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ/ም መነሻውን ከጅቡቲ ያደረገው ተሽከርካሪው አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኝ የነዳጅ ማደያ እንዲያራግፍ የጫነውን ነዳጅ ወደ ሻሸመኔ ከተማ ወስዶ ሊያራግፍ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልፀዋል።
በአሑናዊ የችርቻሮ የነዳጅ ግብይት ዋጋ ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣው ነዳጅ በሕገወጥ መንገድ ወደ ሻሸመኔ ከተማ ሲጓዝ ከሕብረተሠቡ በተሠጠ ጥቆማ መሠረት በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑንም ኢንስፔክተር ቡሎ ዲንሣ ጨምረው ተናግረዋል።
#afromekina
Loading content...
